እኛ በ ሃዋሳ ዩኒሸርሲቲ አዋዳ ካምፓስ የምንኖር የ 2005 ባች ተማሪዎች ስንሆን በ ተለያዩ ፕሮግራሞች ጊዜ የተነሳናቸዉ ፎቶዎች፣ ሺዲዮዎች ና የተለያዩ መጣጥፎች የያዘ ብሎግ ነው።
ማንም ሰው ፎቶዎችም ይሁን ቪዲዮዎችን ማስገባት ይችላል/ትችላለች። በ ፌስቡክ ፔጃችንም ማስገባት ትችላላቹ።
በ ሃዋሳ ዩኒሸርሲቲ አዋዳ ካምፓስ የመጀመሪያዎቹ(የ በኩር) የዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ሰንሆን፣ የ ተላያዩ ችገሮችን ተጋፍጠን ያለፍን እንዲሁም የ ተለያዩ ጥሩ ነገሮችንም ያሳለፍን ተማሪዎች ነን። በ መሆኑም እኛ ጂሲዎች ችግሮችን በ መጋፈጥ እና መልካም ስራዎችን በ መስራት ለ ሌሎች አርአያ የሆንን ና በ ልዩ ፍቅራችን የ ምንታወቅ ዉድ የ አዋደ ልጆች ነን።
እኛ አዋዳን ለ መጀመሪያ ጊዜ የተዋወቅናት በ ጥቅምጥ 28-29 በ 2005 ሲሆን ይሀው እኛን አብባ አፍርታለች።
ስለ አዋዳ
አዋዳ፡ በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ የምትገኝ ቀበሌ ስትሆን የተለያዩ የሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ገጽታ ያላት መልክዓ-ምድር ናት፡፡ ከነዚህ ዉስጥ ሙዝ፣ አቡካዶ፣ ዘይቱን እና ተማሪዎች የሚታጠቡበት ፍልዉሃ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው ፡፡
ካፌ
አዋዳ ካምፓስ በነበርንበት ጊዜ 3 ካፌ ተጠቅመናል
1) ላዊሻ(ፍረሽ) ካፌ
2) ቆርቆሮ(ሲኒየር) ካፌና
3) ብሎኬት(ጂሲ) ካፌ ነው
የተማሪዎች ህብረት
የ ተማሪዎች ህብረት ማለት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት ሲሆን በ ግቢው ህግና ስርዓት የሚቋቋም የተማሪ መማክርት የያዘ ህብረት ማለት ነው የተመሪዎች መማክርት በተማሪዎች የተመረጡ ተማሪዎች ሲሆኑ በተማሪዎች ላይ ለሚደርስ ችግር የቆመ ህብረት ነው ተማሪዎቸመ ሲያጠፉ የሚመክር የሚቀጣ ቅጣቱ ትልቅ ከሆነ ወደ ተማሪዎች አገልግሎት ኃላፊ ያሰተላልፋል
የመጀመሪያ አመት እያለን ጊዜአዊ የተማሪዎች መማክርት ተመርጠው ነበር ከ 2ኛአመት ጀምሮ ግን ለሁለት አመት ቋሚ መማክርት ተመርጠው እያገለገሉ ነበር
ደስታ እና ሃዘን
በ ሶስት አመታችን ችግሮች እና ደስታዎች አሳልፈናል
ከ ደስታው ስንጀምር በ እግር ኳስ ጨዋታ የ ጸረ ኤቸ አይቪ ፕሮግራም የ ብሄር ብሄረሳቦች ቀን የ ግማሽ አና የሶስተኛ አመታችን ክብረ በአል አና የ ተለያዩ ፐሮገራሞች ሲጠቀሱ ከ ሃዘኑ ደግሞ
ከቀላል የተማሪዎች ዊዝድሮው መሙላት እና መጫር እንዲሁም
ከከባድ ደግሞ የተማሪ ሜሮነ ደስታ ሞት ተጠቃሽ ናቸው
ለመጀመሪያ አዋዳን ከረገጥንበት ጀምሮ እስከ ሶስተኛ አመታችን ከ ሌላው ግቢ አንጻር በ ሰላም እና በ ፍቅር ያጠናቀቅን ምርጥ ተማሪዎቸ ነን
መግቢያ
ከ 1ኛ እስከ 3ኛ አመት
አመት | የተጠራንበት ቀን | ግቢ የምንለቅበት ቀን |
1ኛ አመት | ጥቅምት 28 29 | ሃምሌ 14- 18 ፣ 2005 |
2ኛ አመት | ጥቅምጥ 23 24 | ሰኔ 20 -22 ፣ 2006 |
3ኛ አመት | ጥቅምጥ 3 4 |
...
No comments:
Post a Comment